ኤርምያስ 51:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንቺ እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፣ በአንቺ ገበሬውንና በሬውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ ገዦችንና ባለሥልጣኖችን እሰባብራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ገዢዎችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እረኛውንና መንጋውን፥ ገበሬውንና ጥማድ በሬዎቹን፥ ገዢዎችንና ታላላቅ ባለሥልጣኖችን ለማጥፋት መሣሪያ አደረግሁሽ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እበትናለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማዱን እበትናለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና መሳፍንትን እበትናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አለቆችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ። |
ባለሥልጣኖቿንና ጥበበኞቿን፣ ገዦቿንና መኳንንቷን፣ ጦረኞቿንም አሰክራለሁ፤ ለዘላለም ይተኛሉ፤ አይነቁምም፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ።