ስለዚህ የባቢሎናውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠው።
ኤርምያስ 51:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንቺ ወንዱንና ሴቱን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ ሽማግሌውንና ወጣቱን እሰባብራለሁ። በአንቺ ጐረምሳውንና ኰረዳዪቱን እሰባብራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንቺም ወንድንና ሴትን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ጐልማሳውንና ድንግሊቱን እሰባብራለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንቺ ሴቶችንና ወንዶችን ሽማግሌውንና ወጣቱን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ሰባብሬአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንቺም ወንድና ሴትን እበትናለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እበትናለሁ፤ በአንቺም ጐልማሳውንና ቆንጆዪቱን እበትናለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንቺም ሰረገላውንና በላዩ የሚቀመጠውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም ወንድንና ሴትን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም ጐልማሳውንና ቆንጆይቱን እሰባብራለሁ፥ |
ስለዚህ የባቢሎናውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠው።
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብጻውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብጽን ያዋርዳል።
“አሁንም የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ዘር እንዳይቀርላችሁ ወንዶችና ሴቶች፣ ልጆችና ሕፃናት በይሁዳ እንዳይገኙ ለምን እንዲህ ዐይነት ታላቅ ጥፋት በራሳችሁ ላይ ታመጣላችሁ?
ሰይፍ በፈረሰኞቿና በሠረገሎቿ ላይ፣ በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ሁሉ ላይ መጣ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በሀብት ንብረቷ ላይ መጣ! ለዝርፊያም ይሆናሉ።
በእነርሱ ላይ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፤ በውስጤም ልይዘው አልቻልሁም። “መንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናት፣ በተሰበሰቡ ወጣቶችም ላይ አፍስሰው፤ ባልም ሚስትም፣ ያረጁና የጃጁም አያመልጡም።
ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣ በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።
“በየመንገዱ ዐቧራ ላይ፣ ወጣትና ሽማግሌ በአንድነት ወደቁ፤ ወይዛዝርቴና ጐበዛዝቴ፣ በሰይፍ ተገደሉ፤ በቍጣህ ቀን ገደልሃቸው፤ ያለ ርኅራኄም ዐረድሃቸው።
ሽማግሌውን፣ ጕልማሳውንና ልጃገረዲቱን፤ ሴቶችንና ሕፃናትን ፈጽማችሁ አጥፉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ያለበትን ሰው አትንኩ፤ ከቤተ መቅደሴም ጀምሩ።” ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ከነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።
አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንና ሴቱን፣ ልጁንና ሕፃኑን፣ የቀንድ ከብቱንና በጉን፣ ግመሉንና አህያውን ግደል።’ ”