ኤርምያስ 5:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኗል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሠቃቂና አስደንጋጭ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኖአል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሠቃቂና አስደንጋጭ የሆነ ነገር በዚህች ምድር ላይ ተፈጽሞአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምትሰቀጥጥና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፥ |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ አሕዛብን፣ ‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ። ድንግሊቱ እስራኤል፣ እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።
በኢየሩሳሌም ባሉ ነቢያትም ላይ፣ የሚዘገንን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በመዋሸትም ይኖራሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ፣ የክፉዎችን እጅ ያበረታሉ፤ በእኔ ዘንድ ሁሉም እንደ ሰዶም፣ ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ናቸው።”