ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።
ኤርምያስ 48:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉኛ እያለቀሱ፣ ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ ወደ ሖሮናይም ቍልቍል ይወርዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሉሒት አቀበት መራር ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም ቁልቁለት የጥፋትንና የጣርን ጩኸት ሰምተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሉሒት ሲወጡ ምርር ብለው እያለቀሱ ይወጣሉ፤ ወደ ሖሮናይም ቊልቊለት ሲወርዱ በውድመቱ ምክንያት የጭንቀት ድምፅ ያሰማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሎዊት ዓቀበት ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም መንገድ የመባባትን ጩኸት ሰምተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሉሒት ዓቀበት ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም ቍልቍለት የጥፋትንና የመባባትን ጩኸት ሰምተዋል። |
ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።