ኤርምያስ 48:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤ ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እንደ ንስር ይበርራል ክንፉንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክንፉን ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወረወር ንስር በሞአብ ላይ የሚያንዣብብ ጠላት መምጣቱን እግዚአብሔር ተናገረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ እንደ ንስር ይበርራል፤ ክንፉንም በሞአብ ላይ ይዘረጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እንደ ንስር ይበርራል ክንፉንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል። |
በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።
እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ ዐማኑኤል ሆይ! የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።”
እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድባታል፤ ክንፎቹንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያ ቀን የኤዶም ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።
እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ትልቅ ክንፍና ረዥም ማርገብገቢያ ያለው እንዲሁም አካሉ በላባ የተሸፈነ መልኩ ዝንጕርጕር የሆነ ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጥቶ የዝግባ ዛፍ ጫፍ ያዘ፤
“የመጀመሪያው፣ አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ተመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግሩ እንዲቆም ከምድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ የሰውም ልብ ተሰጠው።
ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው። ፈረሰኞቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ ከሩቅ ስፍራም ይመጣሉ። ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ፤