ኤርምያስ 48:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣ ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣ ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኩራቱም ስለ እብሪቱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብ በከፍተኛ ኲራት፥ ራሷን ከፍ ከፍ በማድረግ በትዕቢተኛነት፥ በመጀነንና በልበ ደንዳናነት የተወጠረች መሆንዋን ሰምቼአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞአብን ስድብ፥ የተዋረደውንም ብዙ ውርደቱን፥ ልቡናውንም ያስታበየበትን ትዕቢቱን ሰምተናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኵራቱም ስለ መጓደዱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል። |
የሰማይ አምላክ የሚያደርገው ሁሉ ትክክል፣ መንገዶቹም ሁሉ ጽድቅ ስለ ሆኑ፣ አሁንም እኔ ናቡከደነፆር እርሱን አወድሰዋለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ አከብረዋለሁም፤ እርሱም በትዕቢት የሚመላለሱትን ማዋረድ ይችላል።