ይህን የማደርገውም እኔን ትተው የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፣ የሞዓብን አምላክ ካሞሽን፣ የአሞናውያንን አምላክ ሚልኮምን ስላመለኩ እንዲሁም አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ስላልሄዱ፣ በፊቴ ትክክለኛውን ነገር ስላላደረጉ፣ ሥርዐቴንና ሕጌን ስላልጠበቁ ነው።
ኤርምያስ 48:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ቤት፤ በቤቴል ታምኖ እንዳፈረ ሁሉ፣ ሞዓብም በካሞሽ ያፍራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ቤት መተማመኛቸው በነበረችው በቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞዓብ በካሞሽ ያፍራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ይታመኑበት በነበረው በቤቴል በተተከለው ጣዖት እንዳፈሩ፥ ሞአባውያንም ከሞሽ ተብሎ በሚጠራው ጣዖታቸው ያፍራሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ቤት ይታመንባት ከነበረው ከቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞአብ ከካሞሽ ታፍራለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ቤት ይታመንባት ከነበረው ከቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞዓብ ከካሞሽ ያፍራል። |
ይህን የማደርገውም እኔን ትተው የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፣ የሞዓብን አምላክ ካሞሽን፣ የአሞናውያንን አምላክ ሚልኮምን ስላመለኩ እንዲሁም አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ስላልሄዱ፣ በፊቴ ትክክለኛውን ነገር ስላላደረጉ፣ ሥርዐቴንና ሕጌን ስላልጠበቁ ነው።
ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ባለው ተራራ ላይ ለአስጸያፊው የሞዓብ አምላክ ለካሞሽ እንዲሁም አስጸያፊ ለሆነው ለአሞናውያን አምላክ ለሞሎክ ማምለኪያ ኰረብታ ሠራ።
ከዚያም ኤልያስ፣ “የበኣልን ነቢያት ያዟቸው! አንድም ሰው እንዳያመልጥ” ሲል አዘዘ፤ ሕዝቡም ያዟቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ አውርዶ አሳረዳቸው።
የእግዚአብሔርም ቍጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፤ ነቢይንም ላከበት፤ ነቢዩም፣ “የገዛ ሕዝባቸውን ከእጅህ ማዳን ያልቻሉትን የአሕዛብን አማልክት ርዳታ የጠየቅኸው ለምንድን ነው?” አለው።
“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንተ ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።
ስለዚህ ዕቃውን የሚገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር። “እነርሱም ይደፉታል፤ ዕቃውን ባዶ ያስቀራሉ፤ ማንቈርቈሪያዎቹንም ይሰባብራሉ።
“እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ! ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ! ሞዓብ የመሰደቢያ፣ በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”
አምላክህ ካሞሽ የሰጠህን ይዞ ማቈየቱ ያንተ ፈንታ ነው፤ እኛም እንደዚሁ አምላካችን እግዚአብሔር የሰጠንን ሁሉ ርስት አድርገን እንወርሳለን።