ኤርምያስ 48:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብ ከብላቴንነቱ ጀምሮ ተረጋግቷል፥ በአምቡላውም ላይ ዐርፎአል፥ ከዕቃም ወደ ዕቃ አልተንቈረቈረም፥ ወደ ምርኮም አልሄደም፤ ስለዚህ ቃናው በእርሱ ውስጥ ቀርቶአል፥ መዓዛውም አልተለወጠም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዕቃ ወደ ዕቃ ሳይገለባበጥ ከአተላው ጋር አብሮ የቈየ የወይን ጠጅ ጣዕሙ እንዳለ ይቈያል፤ መዓዛውም አይለወጥም፤ እንደዚሁም የሞአብ ሕዝብ አገራቸው ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ሳይታወኩ ኖረዋል፤ ተማርከውም አይታወቁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሞአብ ከልጅነቷ ጀምራ ዐረፈች፤ በክብርዋም ቅምጥል ነበረች፤ ወይንዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ ወደ ምርኮም አልሄደችም፤ ስለዚህ ቃናው በእርስዋ ውስጥ ቀርቶአል፤ መዓዛዋም አልተለወጠም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ቅምጥል ነበረ፥ በአምቡላውም ላይ ዐርፎአል፥ ከዕቃውም ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፥ ወደ ምርኮም አልሄደም፥ ስለዚህ ቃናው በእርሱ ውስጥ ቀርቶአል፥ መዓዛውም አልተለወጠም። |
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።
ስለዚህ ዕቃውን የሚገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር። “እነርሱም ይደፉታል፤ ዕቃውን ባዶ ያስቀራሉ፤ ማንቈርቈሪያዎቹንም ይሰባብራሉ።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላን፣ አድቅቆ ፈጨን፤ እንደ ባዶ ማድጋ አደረገን፤ እንደ ዘንዶ ዋጠን፣ እንደ ጣፋጭ በልቶን ሆዱን ሞላ፤ በኋላም አንቅሮ ተፋን፤
አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣ የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም፣ እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ፣ እግዚአብሔር የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል።
በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ተንደላቅቀው የሚኖሩትን፣ በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣ ‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።