ኤርምያስ 47:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ ቀኑ ደርሷልና። እግዚአብሔር በቀፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋ ተነሥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለመደምሰስ የተረፉትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለማጥፋት ስለሚመጣው ቀን ነው፤ ጌታ ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ትሩፍ ያጠፋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮስንና ሲዶናን የቀሩትንም ረዳቶቻቸውን ታጠፋ ዘንድ ስለምትመጣው ቀን ነው፤ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንንና በከፍቶር ደሴት የቀሩትን ያጠፋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የቀሩትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ይቈርጥ ዘንድ ስለሚመጣው ቀን ነው፥ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ቅሬታ ያጠፋልና። |
በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
በር ሆይ፤ ዋይ በል! ከተማ ሆይ፤ ጩኽ! ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ ሁላችሁም በፍርሀት ቅለጡ! ጢስ ከሰሜን መጥቶብሃል፤ ከሰልፉ ተነጥሎ የሚቀር የለምና።
በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።”
ያ ቀን ግን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን። ሰይፍ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ ጥማቱም እስኪረካ ድረስ ደም ይጠጣል። በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና።
የታለመልህ የሐሰት ራእይ፣ የተነገረልህ የውሸት ሟርት ቢኖርም፣ የግፍ ጽዋቸው በሞላ፣ ቀናቸው በደረሰ፣ መታረድ በሚገባቸው ክፉዎች፣ ዐንገት ላይ ይሆናል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ክንዴን በፍልስጥኤማውያን ላይ አነሣለሁ፤ ከሊታውያንንም እቈርጣለሁ፤ በባሕሩ ጠረፍ ላይ የቀሩትንም አጠፋለሁ።
የቅጣት ቀን መጥቷል፤ የፍርድም ቀን ቀርቧል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ቂል፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሯል።
“እናንተ እስራኤላውያን፣ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር “እስራኤልን ከግብጽ፣ ፍልስጥኤማውያንን ከቀፍቶር፣ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?
እስከ ጋዛ ድረስ ባሉት መንደሮች የኖሩትን ኤዋውያን በተመለከተም፣ ከቀፍቶር ወጥተው የመጡት ከቀፍቶሪማውያን፣ እነርሱን አጥፍተው መኖሪያቸውን እዚያው አደረጉ።
ካህኑ ፊንሐስና የእስራኤላውያን የጐሣ መሪዎች የነበሩት የማኅበረ ሰቡ አለቆች የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ወገኖች ያሉትን በሰሙ ጊዜ ተደሰቱ።