ኤርምያስ 41:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስማኤል ከምጽጳ ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ሁሉ አምልጠው ወደ ቃሬያ ልጅ ወደ ዮሐናን ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስማኤልም ከምጽጳ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ዘወር ብለው ተመለሱ፥ ወደ ቃሬያም ልጅ ወደ ዮሐናን ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መለስ ብለውም በመሮጥ ከእነርሱ ጋር ተደባለቁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስማኤልም ከመሴፋ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ተመልሰው ወደ ቃርሔም ልጅ ወደ ዮሐናን ሔዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስማኤልም ከምጽጳ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ዘወር ብለው ተመለሱ፥ ወደ ቃሬያም ልጅ ወደ ዮሐናን ሄዱ። |
ደግሞም በምሥራቅና በምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ ፌርዛውያንና በኰረብታማው አገር ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን፣ እንዲሁም ደግሞ በምጽጳ ምድር በአርሞንዔም ተራራ ግርጌ ወዳሉት ወደ ኤዊያውያን ነገሥታት መልእክት ላከ።