ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ” አለው።
ኤርምያስ 30:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃላት ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የነገርኩህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ። |
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ” አለው።
ኤርምያስም ሌላ ብራና ወስዶ ለኔርያ ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ ባሮክም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ባቃጠለው ብራና ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ ጻፈበት፤ ብዙ ተመሳሳይ ቃልም ተጨመረበት።
ዳንኤል ሆይ፤ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ፤ ዐትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ፤ ዕውቀትም ይበዛል።”
ድምፁም፣ “የምታየውን በጥቅልል መጽሐፍ ጽፈህ በኤፌሶን፣ በሰምርኔስ፣ በጴርጋሞን፣ በትያጥሮን፣ በሰርዴስ፣ በፊላድልፍያና በሎዶቅያ ወደሚገኙት ወደ ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ላክ” አለ።