ኤርምያስ 3:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የጌታን ድምፅ አልሰማንምና፥ በእፍረታችን እንጋደም፥ ውርደታችንም ይሸፍነን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛና የቀድሞ አባቶቻችን በመደጋገም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔር አምላካችንን አሳዝነናል፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸምንም፤ ስለዚህ በዕፍረት ልንወድቅና ውርደትም እንደ ልብስ ሊሸፍነን ይገባል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን እንጋደም፥ ውርደታችንም ይክደነን። |
አልሰማህም ወይም አላወቅህም፤ ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤ አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።
አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣ የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣ በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤ ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ። እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤ በሥቃይም ትጋደማላችሁ።
ይሁዳ ሆይ፤ የአማልክትህ ቍጥር የከተሞችህን ብዛት ያህል ነው፤ አሳፋሪ ለሆነው ጣዖት፣ ለበኣል ማጠኛ የሠራችኋቸው መሠዊያዎቻችሁ ብዛት የኢየሩሳሌምን መንገዶች ያህል ነው።’
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤ በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን።
ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣ እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣ በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣ በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣ እንዴት እንደ ተከተልሽኝ አስታውሳለሁ።
በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅሽ፣ ክብርሽንም ለእንግዶች አማልክት፣ በየለምለሙ ዛፍ ሥር አሳልፈሽ በመስጠት፣ ለእኔ ባለመታዘዝሽ፣ በደለኛ መሆንሽን ይህን አንድ ነገር ብቻ እመኚ’ ” ይላል እግዚአብሔር።
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።
ለመሆኑ ይህን የሚያደርጉት እኔን ለማስቈጣት ነውን? ይላል እግዚአብሔር፤ ይልቁን ይህን በማድረጋቸው በሚደርስባቸው ዕፍረት የሚጐዱት ራሳቸውን አይደለምን?
ለምን እዚህ እንቀመጣለን? በአንድነት ተሰብሰቡ! ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ፤ በዚያም እንጥፋ! በርሱ ላይ ኀጢአትን ስላደረግን፣ እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል፤ የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ ሰጥቶናል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእኔ ላይ ወደ ዐመፀው፣ ወደ ዐመፀኞቹ የእስራኤል ልጆች እልክሃለሁ፤ እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐምፀውብኛል።
እንደ ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ አይቀርቡም፤ ወይም ቅዱስ ወደ ሆነው ነገሬ ሁሉ፣ ወይም እጅግ ወደ ተቀደሱ መሥዋዕቶቼ አይቀርቡም፤ የአስጸያፊ ድርጊታቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ።
“እስራኤልን ማግኘቴ፣ የወይንን ፍሬ በምድረ በዳ የማግኘት ያህል ነበር፤ አባቶቻችሁንም ማየቴ፣ የመጀመሪያውን የበለስ ፍሬ የማየት ያህል ነበር፤ ወደ በኣል ፌጎር በመጡ ጊዜ ግን፣ ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ራሳቸውን ለዩ፤ እንደ ወደዱትም ጣዖት የረከሱ ሆኑ።
“እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣ በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና። ደማቸው እንደ ትቢያ፣ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይጣላል።
እናንተም ከዚህች ምድር ነዋሪዎች ጋራ ቃል ኪዳን አታድርጉ፤ መሠዊያቸውንም አፍርሱ፤’ እናንተ ግን አልታዘዛችሁኝም፤ ይህን ያደረጋችሁት ለምንድን ነው?