ከዚያም አብርሃም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ እንደ ገናም ልጅ ለመውለድ በቍ።
ኤርምያስ 27:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነተኞች ነቢያት ከሆኑና በርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ካላቸው፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ ወደ ሰራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር እስኪ ይማልዱ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የጌታም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በጌታ ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይሄዱ እስቲ ወደ ሠራዊት ጌታ ይማለሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ነቢያት ከሆኑና እኔም የሰጠኋቸው የትንቢት ቃል በእነርሱ ዘንድ ካለ፥ ገና ያልተወሰደው በቤተ መቅደስ፥ በይሁዳ ቤተ መንግሥትና በኢየሩሳሌም የቀረው ዕቃ ሁሉ ወደ ባቢሎን እንዳይወሰድ አደርግ ዘንድ እየተማጠኑ ሁሉን ቻይ የሆንኩትን እኔን እግዚአብሔርን ይጠይቁኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይሄዱ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይማለሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀረችው ዕቃ ወደ ባቢሎን እንዳትሄድ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይማለሉ። |
ከዚያም አብርሃም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ እንደ ገናም ልጅ ለመውለድ በቍ።
ከዚያ እናንተ የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶ በእሳት የሚመልሰውም እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው።” ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “ያልኸው መልካም ነው” አሉ።
ስለዚህ የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁት። ከዚያም ከጧት እስከ እኩለ ቀን የበኣልን ስም ጠሩ፤ “በኣል ሆይ ስማን” እያሉ ጮኹ፤ ድምፅ ግን የለም፤ የሚመልስ አልነበረም፤ በሠሩት መሠዊያ ዙሪያም እየዘለሉ ያሸበሽቡ ነበር።
የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን? እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤ ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣ በፊትህ ቆሜ፣ ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ።
ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ቀድሞ ብዙዎች ነበርን አሁን እንደምታየን ግን የቀረነው ጥቂት ነን፤ ስለዚህ እባክህ ልመናችንን ስማ፤ ለዚህ ለተረፈው ሕዝብ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።
“አሁን ግን እንዲራራልን እግዚአብሔርን ለምኑ፤ እንደዚህ ዐይነቱን መሥዋዕት ይዛችሁ ስትቀርቡ ይቀበላችኋልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፣ “ሌላው በደላችን ሳያንስ፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት ስላደረግን እንዳንሞት፣ ለአገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት።
ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት እግዚአብሔርን መበደል ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።