እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የቤተ መንግሥቱን ሀብት በሙሉ አጋዘ፤ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያሠራቸውንም የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ።
ኤርምያስ 27:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልሁ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ ከባቢሎን ቶሎ ይመለሳል’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሟቸው፤ የሚነግሯችሁ የሐሰት ትንቢት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛን ትንቢት ለእናንተ በመናገር፦ ‘እነሆ፥ የጌታ ቤት ዕቃዎች በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳሉ’ ብለው ትንቢት የሚነግሩአችሁን የነብዮቻችሁን ቃላት አትስሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ለካህናቱና ለሕዝቡ እንዳስታውቅ እግዚአብሔር የሚከተለውን ነገረኝ፤ እንዲህ ብዬም ነገርኳቸው፦ “ ‘የቤተ መቅደሱ ዕቃ ሁሉ ከባቢሎን ተመልሶ በፍጥነት ይመጣል’ እያሉ የሚነግሩአችሁን ነቢያት ሁሉ አትስሙአቸው፤ እነርሱ የሚናገሩት የሐሰት ትንቢት ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛውን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳል የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛውን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳል የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ። |
እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የቤተ መንግሥቱን ሀብት በሙሉ አጋዘ፤ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያሠራቸውንም የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ።
ጌታም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካሉት ዕቃዎች ከጥቂቶቹ ጋራ በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ ወደ አምላኩ ቤት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ በአምላኩም ግምጃ ቤት ውስጥ አኖራቸው።