በዚህች ከተማ የሚቈይ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በመቅሠፍት ይሞታል፤ ወጥቶ ለከበቧችሁ ባቢሎናውያን እጁን የሚሰጥ ግን ነፍሱን ያተርፋል፤ በሕይወትም ይኖራል።
ኤርምያስ 27:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች ዐንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ማንኛውንም ሕዝብ በገዛ ምድሩ እንዲቀርና እያረሰም በዚያ እንዲኖር አደርገዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።” ’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተወዋለሁ፤ እነርሱም ያርሱአታል ይቀመጡባታልም፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር ሆኖ የሚገዛለትና የሚያገለግለው ሕዝብ በገዛ ምድሩ እያረሰ እንዲኖር እፈቅድለታለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚገዛለትን ሕዝብ በሀገሩ ላይ እተወዋለሁ፤ እርሱም ያርሳታል፤ ይቀመጥባትማል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚገዛለትን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተወዋለሁ፥ እነርሱም ያርሱአታል ይቀመጡባትማል። |
በዚህች ከተማ የሚቈይ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በመቅሠፍት ይሞታል፤ ወጥቶ ለከበቧችሁ ባቢሎናውያን እጁን የሚሰጥ ግን ነፍሱን ያተርፋል፤ በሕይወትም ይኖራል።
ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ይህንኑ መልእክት እንዲህ ብዬ ነገርሁት፤ “ዐንገታችሁን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች ዝቅ አድርጉ፤ እርሱንና ሕዝቡን አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
“ ‘ “ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር የማይገዛ፣ ዐንገቱንም ከቀንበሩ በታች ዝቅ የማያደርግ ማንኛውንም ሕዝብ ወይም መንግሥት በእጁ እስከማጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሠፍትም እቀጣዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዚህች ከተማ የሚቀር ሁሉ በሰይፍ፣ በራብ ወይም በቸነፈር ይሞታል፤ ይህን ስፍራ ለቅቆ ወደ ባቢሎናውያን የሚሄድ ሁሉ ይተርፋል፤ ያመልጣል፤ በሕይወትም ይኖራል።’
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤልን ሕዝብ ከተበተኑባቸው አገሮች መካከል በምሰበስብበት ጊዜ፣ አሕዛብ እያዩ ቅድስናዬን በመካከላቸው እገልጣለሁ፤ ከዚያም በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ፤ ይህም ለባሪያዬ ለያዕቆብ የሰጠሁት ነው።