ስለዚህም እግዚአብሔር፣ “የፈጠርሁትን የሰው ዘር ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት እስከ ሰማይ ወፎች አጠፋለሁ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
ኤርምያስ 21:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህች ከተማ የሚኖሩትን፣ ሰዎችንም ሆኑ እንስሳትን እመታለሁ፤ እነርሱም በታላቅ መቅሠፍት ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፥ በጽኑም ቸነፈር ይሞታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ እመታለሁ፤ ሰዎችና እንስሶች በአንድነት በአሠቃቂ ወረርሽኝ ያልቃሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፤ በጽኑም ቸነፈር ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፥ በጽኑም ቸነፈር ይሞታሉ። |
ስለዚህም እግዚአብሔር፣ “የፈጠርሁትን የሰው ዘር ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት እስከ ሰማይ ወፎች አጠፋለሁ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤
ቢጾሙም ጩኸታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ቢያቀርቡም አልቀበላቸውም፤ ነገር ግን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር አጠፋቸዋለሁ።”
“በአደገኛ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩም፤ በምድርም ላይ እንደ ጕድፍ ይጣላሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘አንተንና ወዳጆችህ ሁሉ ለሽብር እዳርጋለሁ፤ የገዛ ዐይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ። ይሁዳን ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።
“እነሆ፤ ከተማዪቱን ለመያዝ የዐፈር ድልድል በዙሪያዋ ተሠርቷል፤ ከሰይፍ፣ ከራብና ከቸነፈር የተነሣ ከተማዪቱን ለሚወጓት ለባቢሎናውያን ዐልፋ ልትሰጥ ነው፤ እንደምታየውም የተናገርኸው እየተፈጸመ ነው።
“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰውም ሆነ እንስሳት በማይኖሩበት በዚህ ባዶ ስፍራ፣ በከተማዎቹም ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት እንደ ገና ያገኛሉ።
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለወንድሞቻችሁና ለወገኖቻችሁ ነጻነት አላወጃችሁምና አልታዘዛችሁኝም። እንግዲህ እኔ ነጻነት ዐውጅላችኋለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘ይኸውም በሰይፍ፣ በቸነፈርና በራብ የምትወድቁበት ነጻነት ነው። ለምድር መንግሥታት ሁሉ መሠቀቂያ አደርጋችኋለሁ።
ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይህችን ምድር፣ በርሷም ላይ የሚኖሩትን ሰዎችንና እንስሳትን ያጠፋል በማለት የጻፍህበት ለምንድን ነው?” ብለህ ብራናውን አቃጥለሃል።
“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ በሰውና በእንስሳ ላይ፣ በዱር ዛፍና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።
ነገር ግን በሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ስለ ጸያፍ ተግባራቸው ይናገሩ ዘንድ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ከሰይፍ ከራብና ከቸነፈር አተርፋለሁ። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
“የሰው ልጅ ሆይ፤ አንድ አገር በእኔ ባለ መታመን ቢበድለኝና እኔም እጄን በላዩ ዘርግቼ የምግብ ምንጩን ባደርቅ፣ ራብንም አምጥቼበት ሰውንና እንስሳቱን ብገድል፣
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ሰውንና እንስሳቱን ለማጥፋት አራቱን አስፈሪ ፍርዶቼን፦ ሰይፍን፣ ራብን፣ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በኢየሩሳሌም ላይ በማመጣበት ጊዜ ምንኛ የከፋ ይሆን!
“እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ በፍርስራሾች ውስጥ የተረፉት በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በገጠር ያሉትን ቦጫጭቀው እንዲበሏቸው ለዱር አራዊት እሰጣቸዋለሁ፤ በምሽግና በዋሻ ያሉትም በቸነፈር ይሞታሉ።
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት፣ ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ የቤተ መቅደሱም ኰረብታ ዳዋ የወረሰው ጕብታ ይሆናል።
“ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎች፣ የባሕርንም ዓሦች አጠፋለሁ፤ ለክፉዎችም እንቅፋት የሆኑትን ጣዖታት አጠፋለሁ።” “ማንኛውንም ሰው ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ” ይላል እግዚአብሔር።