ይህ ቤተ መቅደስ አሁን እጅግ የሚያስደንቅ ቢሆንም እንኳ፣ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ እያፌዘም፣ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያደረገው ስለ ምን ይሆን?’ ይላል፤
ኤርምያስ 19:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህችን ከተማ ድምጥማጧን አጠፋለሁ፤ የድንጋጤና መሣለቂያም ምልክት አደርጋታለሁ፤ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ከቍስሎቿም የተነሣ ወይ ጉድ! ይላሉ፣ ያሾፋሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህችንም ከተማ ለመሣቀቂና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ የሚያልፍባትም ሁሉ ይሣቀቃል፥ ስለ ተደረገባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህችን ከተማ የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነግጣል፤ በደረሰባት ችግርም ይገረማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህችንም ከተማ ለጥፋትና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ በእርስዋም የሚያልፍ ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነግጣል፤ ያፍዋጫልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህችንም ከተማ ለመደነቂያና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነቃል ከንፈሩንም ይመጥጣል። |
ይህ ቤተ መቅደስ አሁን እጅግ የሚያስደንቅ ቢሆንም እንኳ፣ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ እያፌዘም፣ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያደረገው ስለ ምን ይሆን?’ ይላል፤
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ባድማና ሰዎች የሚጸየፏቸው መዘባበቻና ርግማን እንዲሆኑ፣ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታቷንና ባለሥልጣኖቿን፣
ባሶራ ፈራርሳ የድንጋጤ፣ የመዘባበቻና የርግማን ምልክት እንደምትሆን በራሴ ምያለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከተሞቿም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።”
ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ፣ የሚኖርባት አይገኝም፤ በቍስሎቿም ሁሉ ምክንያት፣ በባቢሎን የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ ያፌዝባታልም።
የዖምሪን ሥርዐት፣ የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤ ትውፊታቸውንም ተከትለሃል። ስለዚህ አንተን ለውድመት፣ ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ አሕዛብም ይሣለቁብሃል።”
ያለ ሥጋት የኖረች፣ ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤ እርሷም በልቧ፣ “እኔ ብቻ ነኝ! ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣ ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣ ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።
የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሪቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና እግዚአብሔር ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ።