ኤርምያስ 16:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ሁሉ ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ ሰዎቹ፣ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ ለምን ዐወጀ? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኀጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቁህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃላት ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ‘ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ለምን ጌታ ተናገረብን? በደላችንስ ምንድነው? በአምላካችንስ በጌታ ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድነው?’ ቢሉህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህን ሁሉ በምትነግራቸው ጊዜ ‘እግዚአብሔር በእኛ ላይ ይህን የሚያኽል ከባድ ጥፋት ለምን ወሰነብን? ምን በደልን? በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊትስ የሠራነው ኃጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቁሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ኀጢአት ምንድን ነው? ቢሉህ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድር ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድር ነው? ቢሉህ፥ |
“ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽ ራስሽን ብትጠይቂ፣ ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣ በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።
“ ‘አልረከስሁም፣ በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽ እስኪ አስቢ፣ ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤ እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤
ይህም የሆነው ስላደረጉት ክፋት ነው። እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ ላላወቋቸው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ አስቈጥተውኛል።
ሕዝቡ፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ሁሉ ነገር ለምን አደረገብን?’ ብለው ቢጠይቁ፣ ‘እኔን፣ እንደ ተዋችሁኝና በራሳችሁ ምድር ባዕዳን አማልክትን እንዳገለገላችሁ፣ እንደዚሁ የእናንተ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።
ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤ “እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤ ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣ ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”