ሁሉም ሰው ጅልና ዕውቀት የለሽ ነው። የወርቅ አንጥረኛው ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤ የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤ እስትንፋስም የላቸውም።
ኤርምያስ 10:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኞቹ አእምሮ የላቸውም፤ እግዚአብሔርን አይጠይቁም፤ ስለዚህ አልተከናወነላቸውም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበታትነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እረኞች ቂላ ቂል ሆነዋልና፥ ጌታንም አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፥ “መሪዎቻችን ሞኞች ከመሆናቸው የተነሣ፥ የእግዚአብሔርን ርዳታ አልጠየቁም፤ ውድቀት የደረሰባቸውና ሕዝባችንም ተበትኖ የቀረው ስለዚህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እረኞች አእምሮአቸውን አጥተዋልና፥ እግዚአብሔርንም አልፈለጉትምና፤ ስለዚህም መሰማሪያውን አላወቁም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል። |
ሁሉም ሰው ጅልና ዕውቀት የለሽ ነው። የወርቅ አንጥረኛው ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤ የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤ እስትንፋስም የላቸውም።
‘እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው ካህናቱ አልጠየቁም፤ ከሕጉ ጋራ የሚውሉት አላወቁኝም፤ መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤ ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤ ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”
ግመሎቻቸው ይዘረፋሉ፤ ከብቶቻቸውንም አንጋግተው ይነዱባቸዋል፤ ጠጕሩን የሚቀነብበውን ወገን እበትናለሁ፤ ከየአቅጣጫው መዓት አመጣባችኋለው።” ይላል እግዚአብሔር።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”
“እስራኤል አንበሶች ያሳደዱት፣ የተበተነ መንጋ ነው፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ፣ ቦጫጭቆ በላው፤ በኋላም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ ዐጥንቱን ቈረጣጠመው።”
እረኛ ከመንጋው ጋራ ሳለ፣ የተበተኑበትን በጎች እንደሚፈልግ ሁሉ፣ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ። በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።
“ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዷል፤ መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ መንጋውን የይሁዳ ቤት ይጐበኛልና፤ በጦርነትም ጊዜ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣ በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ! እረኛውን ምታ፣ በጎቹም ይበተናሉ፤ እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”