ያዕቆብ 4:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገ የሚሆነውን እንኳ አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድን ናት? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገ የሚሆነውን አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድነው? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት አይደላችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገ የሚሆነውን አታውቁም፤ ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ለአንድ አፍታ ታይቶ በኋላ እንደሚጠፋ ጉም ናችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። |
ቤቴ እንደ እረኛ ድንኳን ተነቀለ፤ ከእኔም ተወሰደ፤ ሕይወቴን እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፤ ከመጠቅለያ ቈርጦኛል፤ ከጧት እስከ ማታ ልትጨርሰኝ ፈጠንህ።
ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል፣ “ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤