ኢሳይያስ 66:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእኔ በሬ ሲሠዉ በሌላ በኩል የሰውን ሕይወት ያጠፋሉ፤ ለእኔ ጠቦት ሲሠዉ ለጣዖትም ውሻ ያቀርባሉ፤ ለእኔ የእህል መሥዋዕት ሲያቀርቡ፤ የዕሪያ ደምም ለጣዖት ያቀርባሉ፤ ለእኔ ዕጣን ያጥናሉ፤ ጣዖቶቻቸውንም ያመሰግናሉ፤ የራሳቸውን አካሄድ በመምረጥ በርኲሰታቸው ይደሰታሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፥ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፥ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፥ እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፥ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል፥ |
ማንም ቆም ብሎ አላሰበም፤ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ስለሌለው እንዲህ ማለት አልቻለም፤ “ግማሹን በእሳት አቃጥዬዋለሁ፤ በፍሙ እንጀራ ጋግሬበታለሁ፤ ሥጋ ጠብሼበት በልቻለሁ፤ ታዲያ፣ በቀረው እንዴት ጸያፍ ነገር እሠራለሁ? ለግንድስ መስገድ ይገባኛልን?”
ተጣርቼ ስላልመለሳችሁ፣ ተናግሬ ስላልሰማችሁ፣ በፊቴ ክፉ ነገር ስላደረጋችሁ፣ የሚያስከፋኝን ነገር ስለ መረጣችሁ፣ ለሰይፍ እዳርጋችኋለሁ፤ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ።”
ለዐመፀኛ ሕዝብ፣ መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣ የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ። ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣
“ወደ አትክልት ቦታዎች ለመሄድና ከተክሎቹ አንዱን ለማምለክ ራሳቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የዕሪያዎችንና የዐይጦችን ሥጋ፣ የረከሱ ነገሮችንም የሚበሉ ሁሉ የመጨረሻ ፍርዳቸውን በአንድነት ይቀበላሉ” ይላል እግዚአብሔር።
ዕጣን ከሳባ ምድር፣ ጣፋጩ ከሙን ከሩቅ አገር ቢመጣ ምን ይጠቅመኛል? የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን አልቀበልም፤ ሌላውም መሥዋዕታችሁ ደስ አያሰኙኝም።”
ወደ ካህናቱም ወደ አሮን ልጆች ያምጣው። ካህኑ ከላመው ዱቄትና ከዘይቱ አንድ ዕፍኝ ሙሉ ያንሣለት፤ ዕጣኑንም ሁሉ ይውሰደው፤ ይህንም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው።
ከዚያም ሐጌ እንዲህ አለ፤ “ ‘ይህ ሕዝብና ይህ ወገንም በፊቴ እንደዚሁ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የእጃቸው ሥራና የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው።’
ዐሣማም እንደዚሁ ርኩስ ነው፤ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም፣ ስለማያመሰኳ፣ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ።
ለዝሙት ዐዳሪ ሴት ወይም ለወንደቃ የተከፈለውን ዋጋ ለማንኛውም ስእለት አድርገህ ለመስጠት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አታምጣ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።