ሆሴዕ 5:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራቸው ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አልፈቀደላቸውም፤ የአመንዝራ መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ ጌታንም አላውቁምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዝሙት መንፈስ በእስራኤል ሕዝብ ውስጥ ስላለና እግዚአብሔርንም ስለማያውቁ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ሥራቸው አይፈቅድላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ልባቸውን አላቀኑም፤ የዝሙት መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ እግዚአብሔርንም አላወቁትምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ሥራቸውን አላቀኑም፥ የግልሙትና መንፈስ በውስጣቸው አለና፥ እግዚአብሔርንም አላውቁምና። |
እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹም ልባቸውም ወደ እኔ ስለሚመለሱ፣ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
የሚመካ ግን፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በማወቁና፣ በምድር ላይ ምሕረትን፣ ፍትሕንና ጽድቅን የማደርግ መሆኔን በመረዳቱ፣ በዚህ ይመካ፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች፣ እደሰታለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።
በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤ የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣ ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው።
እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።
“ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣ የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ አልቀጣቸውም። ወንዶች ከጋለሞቶች ጋራ ይሴስናሉ፤ ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋራ ይሠዋሉና፤ የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!
ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል። ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣ እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤ የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።