ዘፍጥረት 8:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምድር እስካለች ድረስ፣ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት፣ አይቋረጡም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር እስካለች ድረስ፥ ለመዝራትና ለማጨድ፥ ለብርድና ለሙቀት፥ ለበጋና ለክረምት፥ ለቀንና ለሌሊት የማያቋርጥ ጊዜ ይኖራል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም። |
በቀን እንድታበራ፣ ፀሓይን የመደበ፣ በሌሊት እንዲያበሩ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ያዘዛቸው፣ የሞገዱ ድምፅ እንዲተምም፣ ባሕሩን የሚያናውጥ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ እንዲህ ይላል፤
በልባቸውም፣ ‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣ መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፣ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ።