Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 5:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በልባቸውም፣ ‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣ መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በልባቸውም፦ “የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን ጌታን እንፍራ” አላሉም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በወቅቱ የምሰጣችሁ፥ የመከርንም ወራት በየዓመቱ የማመላልስላችሁ እኔ ነኝ፤ እናንተ ግን እኔን ማክበርን ተዋችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በል​ባ​ቸ​ውም፦ የመ​ከ​ሩ​ንና የበ​ል​ጉን ዝናብ በጊዜ የሚ​ሰ​ጠ​ውን፥ ለመ​ከ​ርም የተ​መ​ደ​ቡ​ትን ወራት የሚ​ጠ​ብ​ቅ​ል​ንን አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ፍራ አላ​ሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በልባቸውም፦ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 5:24
27 Referencias Cruzadas  

ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤ በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።


የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ሐሤት አድርጉ፤ የበልግን ዝናብ፣ በጽድቅ ሰጥቷችኋልና፤ እንደ ቀድሞውም፣ የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል።


“ምድር እስካለች ድረስ፣ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት፣ አይቋረጡም።”


ይሁን እንጂ ዝናብን ከሰማይ እንዲሁም ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠቱ፣ ደግሞም ልባችሁን በመብልና በደስታ በማርካቱ መልካምን በማድረግ ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”


እንደዚህም በማድረጋችሁ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ፀሓዩን ለክፉዎችና ለመልካሞች ያወጣል፤ ዝናቡንም ለኀጢአተኞችና ለጻድቃን ያዘንባል።


ከአሕዛብ ከንቱ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለን? ሰማያትስ በራሳቸው ማካፋት ይችላሉን? አይ! አይችሉም፣ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ነህ፣ ስለዚህም ተስፋችን በአንተ ላይ ነው።


እነዚህ ሰዎች ትንቢት በሚናገሩባቸው ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ለመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ ደግሞም ውሆችን ወደ ደም ለመለወጥ በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ ምድርን በማንኛውም መቅሠፍት ለመምታት ሥልጣን አላቸው።


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፣ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ።


የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣ ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል።


“መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ ሌላው ዝናብ ዐጥቶ ደረቀ።


“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰባብሮናል፤ እርሱም ይጠግነናል፤ እርሱ አቍስሎናል፤ እርሱም ይፈውሰናል።


ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ ፊታቸውንም ወደዚያ ያቀናሉ። መጥተውም ከቶ በማይረሳ፣ በዘላለም ቃል ኪዳን፣ ከእግዚአብሔር ጋራ ይጣበቃሉ።


ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን? ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣ አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።


ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤ አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤ ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤ ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል።


ትቢያ ሲጠጥር፣ ጓሎችም እርስ በርስ ሲጣበቁ፣


በዚህ ጊዜ ከገለዓድ ነዋሪዎች አንዱ የሆነው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፣ “በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር፣ በሚቀጥሉት ዓመታት ዝናብ ወይም ጠል አይኖርም” አለው።


እግዚአብሔር ለምድርህ በወቅቱ ዝናብን ለመስጠትና የእጅህን ሥራ ሁሉ ለመባረክ፣ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትልሃል፤ አንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ እንጂ ከአንዳቸውም አትበደርም።


ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በመጨረሻውም ዘመን በመንቀጥቀጥ ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።


ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል።


ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤ እጅግ ታበለጥጋታለህም። ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤ አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና።


ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣ እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፤ ኋለኛው ዝናብም ጠፋ። አንቺ ግን አሁንም የጋለሞታ ገጽታ አለብሽ፤ ዐይንሽን በዕፍረት አልሰብር ብለሻል።


ዝናብ እንደሚጠብቅ ሰው ጠበቁኝ፤ ቃሌንም እንደ በልግ ዝናብ ጠጡ፤


ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios