ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ።
ዘፍጥረት 7:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋራ ታስገባለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንጹሕ የሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ የሰማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለምግብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረልግልህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትውስዳለህ። |
ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ።
ከዚያም ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያው ላይ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ፣ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት ወፎች የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤