ይሥሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች።
ዘፍጥረት 48:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ መልስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፣ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ ዐዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ፓዳን በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት መንገድ ቀርቶኝ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፥ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ፥ ቀበርኋት፥ እርሷም ቤተልሔም ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመስጴጦምያ ስመለስ በከነዓን ምድር ገና ከኤፍራታ ሳልርቅ እናትህ ራሔል ሞተችብኝ፤ እርስዋን ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።” (ይህችም ኤፍራታ ዛሬ ቤተልሔም ተብላ የምትጠራው ቦታ ነች።) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ከሶርያ መስጴጦምያ በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ቀርቶኝ በፈረስ መጋለቢያው መንገድ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፤ በዚያም በኤፍራታ ወደ ፈረስ መጋለቢያ በሚወስደው መንገድ ላይ ቀበርኋት፤ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ከመስዼጦምያ በመጣሁ ጊዜ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ቀርቶኝ በመንገድ ሳለሁ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት ቀበርኍት። |
ይሥሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች።
“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።”
የሰውየው ስም አሊሜሌክ፣ የሚስቱ ኑኃሚን፣ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበር። እነርሱም የይሁዳ ቤተ ልሔም ኤፍራታውያን ሲሆኑ፣ ወደ ሞዓብ አገር ሄደው በዚያ ኖሩ።
በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ኤፍሬማዊ ሲሆን፣ የኤያሬምኤል ልጅ፣ የኢሊዩ ልጅ፣ የቶሑ ልጅ፣ የናሲብ ልጅ፣ ነበረ።
ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፣ በብንያም ወሰን ላይ በምትገኘው ጼልጻህ በተባለች ስፍራ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፣ ‘የምትፈልጋቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፣ “ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?” እያለ በመጨነቅ ላይ ነው’ ይሉሃል።
ሳሙኤል እግዚአብሔር ያለውን ነገር አደረገ። ቤተ ልሔም እንደ ደረሰም፣ የከተማዪቱ ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡ፣ እነርሱም “አመጣጥህ ለሰላም ነውን?” ብለው ጠየቁት።
ዳዊት በይሁዳ የቤተ ልሔሙ ሰው የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ በሳኦልም ዘመን ያረጀና ዕድሜው የገፋ ሰው ነበር።