አብራምም፣ “አገልጋይሽ እንደ ሆነች በእጅሽ ውስጥ ናት፤ የፈለግሽውን አድርጊባት” አላት። ከዚያም ሦራ ስላሠቃየቻት አጋር ጥላት ኰበለለች።
ዘፍጥረት 45:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ፣ ፈርዖንና ሹማምቱ ሁሉ ደስ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፈርዖንም ቤት፥ “የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ፥” በሰሙትም ነገር ፈርዖንና አገልጋዮቹ ደስ ተሰኙበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ ፈርዖንና ባለሥልጣኖቹ ደስ አላቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፈርዖንም ቤት፥ “የዮሴፍ ወንድሞች መጡ” ተብሎ ወሬ ተሰማ፤ ፈርዖንና ቤተ ሰቡም ሁሉ ደስ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፈርዖን ቤት፦ የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ በዚያውም ፈርዖንና ሎላልቱ ደስ ተሰኙበት። |
አብራምም፣ “አገልጋይሽ እንደ ሆነች በእጅሽ ውስጥ ናት፤ የፈለግሽውን አድርጊባት” አላት። ከዚያም ሦራ ስላሠቃየቻት አጋር ጥላት ኰበለለች።
ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ለወንድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እንዲህ አድርጉ፤ አህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ተመለሱ።
ሚስቱ ዞሳራና ወዳጆቹ በሙሉ፣ “ቁመቱ ዐምሳ ክንድ የሆነ መስቀያ አስተክልና መርዶክዮስ እንዲሰቀልበት በጧት ለንጉሡ ንገረው፤ ከዚያም ደስ ብሎህ ከንጉሡ ጋራ ወደ ግብዣው ግባ” አሉት። ይህም ሐሳብ ሐማን እጅግ ደስ አሠኘው፤ መስቀያውንም አስተከለ።
አባባሉ ሁላቸውን ደስ አሠኘ፤ በእምነትና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን እንዲሁም ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞናን፣ ጰርሜናንና ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ።
በጕዞ ላይ ሳላችሁ የምትሰፍሩባቸውን ቦታዎች ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት እርሱ ሌሊት በእሳት፣ ቀን በደመና ይመራችሁ ነበር።