ዘፍጥረት 36:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራማው አገር በኤዶም ይኖሩ የነበሩት ኤዶማውያን ቅድመ አያት የነበረው የዔሳው ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም እንዲህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው። |
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፤ “ጌታዬን ዔሳውን እንዲህ ትሉታላችሁ፤ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል በሉት፤ “ከላባ ዘንድ ተቀምጬ እስከ አሁን ድረስ እዚያው ኖርሁ፤
ከእነዚሁ ዐምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኰረብታማ አገር ወረሩ።
ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤ መልእክተኛው ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህ ብሏል፤ “ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።”
ከየትኛውም ምድራቸው ላይ ለጫማችሁ መርገጫ ታኽል እንኳ መሬት ስለማልሰጣችሁ፣ ለጦርነት አታነሣሧቸው። ኰረብታማውን የሴይርን አገር ርስት አድርጌ ለዔሳው ሰጥቼዋለሁ።
ለይሥሐቅ ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም ኰረብታማውን የሴይርን ምድር ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብና ልጆቹ ግን ወደ ግብጽ ወረዱ።