ዘፍጥረት 36:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች፥ ባሴማትም ራዑኤልን ወለደች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓዳ ለዔሳው ኤሊፋዝን ወለደችለት፤ ባሴማትም ረዑኤልን ወለደችለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐዳሶ ለእርሱ ኤልፋዝን ወለደች፤ ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ |
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስ፣ ናዕማታዊውም ሶፋር በኢዮብ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ሄደው ሊያስተዛዝኑትና ሊያጽናኑት በመስማማት ከየመኖሪያቸው በአንድነት መጡ።
በዚህ ጊዜ ሙሴ የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፣ “እነሆ፤ እግዚአብሔር፣ ‘እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ጕዞ ጀምረናል፤ በመልካም ሁኔታ ስለምናኖርህ ከእኛ ጋራ ሂድ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል በጎ ነገር ለማድረግ ቃል ገብቷልና አለው።”