ዘፍጥረት 34:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴኬም የተባለው የአገሩ ገዥ የኤዊያዊ የኤሞር ልጅ ባያት ጊዜ ይዞ በማስገደድ ደፈራት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአገሩ ገዢ የሒዋዊው ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት፥ ወሰዳትም ከእርሷም ጋር ተኛ፥ አስነወራትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአገሩ ገዢ የሒዋዊው የሐሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት፤ በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሩ አለቃ የኤዊያዊው ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰዳትም፤ ከእርስዋም ጋር ተኛ፤ አስነወራትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩ አለቃ የኤዊያዊ ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት ወሰዳርም ከእርስዋም ጋር ተኛ አስነወራትም። |
ያዕቆብም ስምዖንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በዚህ አገር በሚኖሩት በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ዘንድ እንደ ጥንብ አስቈጠራችሁኝ፤ ጭንቀትም እንዲደርስብኝ አድርጋችኋል። እኛ በቍጥር አነስተኞች ነን፤ ተባብረው ቢነሡብኝና ቢያጠቁኝ እኔና ቤተ ሰቤ መጥፋታችን አይደለምን?”
አንድ ቀን ማታ፣ ዳዊት ከዐልጋው ተነሥቶ በንጉሥ ቤት ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፣ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ በጣም ውብ ነበረች።
ከዚያም ዳዊት መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ እርሱ ወዳለበት ገባች፤ ዐብሯትም ተኛ። በዚህም ጊዜ ወርኃዊ የመንጻት ጊዜዋን ፈጽማ ነበር። ከዚያም ተመልሳ ወደ ቤቷ ሄደች።
በርሷ ደስተኛ ባትሆን፣ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጣት፤ ውርደት ላይ ጥለሃታልና ልትሸጣት ወይም እንደ ባሪያ ልትቈጥራት አይገባህም።
ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፣ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስገድዶ ስለ ደፈረ፣ ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ።
ሰውየው ለልጅቱ አባት ዐምሳ ሰቅል ብር ይክፈል፤ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሯታልና፣ እርሷን ማግባት አለበት፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።
የእስራኤልም ሰዎች ለኤዊያውያኑ፣ “እናንተ የምትኖሩት እዚሁ ቅርብ ቢሆንስ? ታዲያ ከእናንተ ጋራ እንዴት ቃል ኪዳን እንገባለን?” አሏቸው።
የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩባኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቢሜሌክ እንገዛለን?