ዘፍጥረት 31:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የአባታችሁን የላባን መንጋዎች ወስዶ ለእኔ የሰጠኝ በዚህ ዐይነት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎቹ ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ |
የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያካበተውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ።
“እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ።