La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 27:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ተነሣና ወደ መንጋው ሄደህ ሁለት ፍርጥም ያሉ የፍየል ጠቦቶች አምጣልኝ፤ እኔም አባትህ የሚወድደውን ዐይነት ምግብ አዘጋጅለታለሁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ መንጋ ሄደህ ሁለት መልካም ጠቦቶች አምጣልኝ፥ እነርሱንም ጣፋጭ መብል ለአባትህ እንደሚወደው አደርጋለሁ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አባትህ እንደሚወደው አጣፍጬ ጥሩ ምግብ እንድሠራለት፥ ወደ መንጋዎች ሂድና ሁለት የሰቡ የፍየል ጠቦቶችን አምጣልኝ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ በጎ​ቻ​ችን ሄደህ ሁለት መል​ካም ጠቦ​ቶች አም​ጣ​ልኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለአ​ባ​ትህ እን​ደ​ሚ​ወ​ደው መብል አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱን፥ ጣፋጭ መብል ለአባትህ እንደሚወደው አደርጋለሁ፤

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 27:9
6 Referencias Cruzadas  

እርሱም ከመሞቱ በፊት እንዲመርቅህ ይዘህለት ግባና ይብላ።”


እርሱም ሄዶ ጠቦቶቹን ለእናቱ አመጣላት፤ እርሷም ልክ አባቱ እንደሚወድደው ዐይነት አጣፍጣ ጥሩ ምግብ አዘጋጀችለት።


ከመሞቴ በፊት እንድመርቅህ የምወድደውን ዐይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ አብላኝ።”


ልጄ ሆይ፤ እንግዲህ የምነግርህን በጥሞና ስማኝ፤ የምልህንም አድርግ።


ከዚያም ማኑሄ የእግዚአብሔርን መልአክ፣ “የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይ” አለው።


እሴይም እንጀራና በወይን ጠጅ የተሞላ አቍማዳ በአህያ አስጭኖ፣ የፍየል ጠቦትም አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው።