ዘፍጥረት 27:44 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንድምህ ቍጣ እስከሚበርድ እዚያው ቈይ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጥ፥ የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወንድምህ ቊጣ እስኪበርድ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እዚያው ቈይ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱም ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጥ። የወንድምህ ቍጣ ከአንተ እስኪበርድ ድረስ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱም ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጥ የወንድምህ ቍጣ እስኪበርድ |
ሃያ ዓመት በቤትህ የኖርሁት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ዐሥራ አራት ዓመት ለሁለቱ ልጆችህ ብዬ አገለገልሁ፤ ስድስት ዓመት ስለ መንጋዎችህ ስል አገለገልሁ፤ ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋውጠህብኛል።
ጌታ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ፣ ምድርን ይዳስሳል፤ እርሷም ትቀልጣለች፤ በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ይወርዳል።