እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።
ዘፍጥረት 27:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናቱም፣ “ልጄ ሆይ፤ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይድረስ፤ ግድ የለህም፤ እንደ ነገርሁህ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናቱም አለችው፦ “ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፥ ሂድና አምጣልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናቱም “ልጄ ሆይ፥ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደ ነገርኩህ አድርግ፤ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናቱም አለችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያልሁህን አምጣልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናቱም አለችው፦ ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን ቃሌን ብቻ ስማኝ ሂድና አምጣልኝ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።
ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛው እኔ ልሁን።