ዘፍጥረት 26:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ፣ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። ይሥሐቅም የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ ወደሚኖርበት ወደ ጌራራ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ፥ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቤሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወድ አቢሜሌክ ወደ ግውራራ ሄደ። |
በዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፣ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “አንተና ከግብጽ ያወጣኸው ሕዝብህ ይህን ስፍራ ለቅቃችሁ ‘ለዘርህ እሰጣለሁ’ በማለት ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ተስፋ ወደ ገባሁላችሁ ምድር ሂዱ።
መሳፍንት በሚገዙበት ዘመን፣ በምድሪቱ ላይ ራብ ሆነ፤ አንድ ሰው በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተ ልሔም ሚስቱንና ሁለቱን ወንዶች ልጆቹን ይዞ፣ ለተወሰነ ጊዜ ለመኖር ወደ ሞዓብ አገር ሄደ።