ዘፍጥረት 24:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኅቱ ያደረገችውን የወርቅ ቀለበትና አምባሮች እንዳየ፣ እንዲሁም ርብቃ ሰውየው ያላትን ስትናገር እንደ ሰማ፣ ወዲያውኑ ወደ ሰውየው ሄደ፤ በምንጩም ዳር ከግመሎቹ አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀለበቱንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ “ያ ሰው እንዲህ አለኝ” ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፥ እነሆም፥ በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጒትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ያላትን ስትናገር ስለ ሰማም ነው። እርሱንም በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጉትቻውንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱንም የርብቃን ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፤ እነሆም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀለበቱንን አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ እነሆም በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር። |
እርሱንም “አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ሆይ፤ ና፤ እዚህ ውጭ የቆምኸው ለምንድን ነው? እነሆ፤ ለአንተ ማረፊያ ለግመሎችህም ማደሪያ አዘጋጅቻለሁ” አለው።
“የሚፈነጥዙ ሰዎች ድምፅ በዙሪያዋ ነበር፤ ከሚያውኩ ሰዎች ጋራ ከበረሓ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ፤ በሴትየዋና በእኅቷም ላይ አንባር፣ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው።
እናቱን፣ “አንድ ሺሕ አንድ መቶ ሰቅል ብር ተሰርቆብሽ፣ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት። ከዚያም እናቱ፣ “ልጄ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለችው።