አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ።
ዘፍጥረት 23:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሣራ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሣራም ዕድሜ መቶ ኻያ ሰባት ዓመት ሆነ፥ እነዚህ ሣራ የኖረችባቸው ዓመታት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሣራ መቶ ኻያ ሰባት ዓመት ከኖረች በኋላ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሣራም ዕድሜ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሣራም ዕድሜ መቶ ሀያ ሰባት ዓመት ሆነ። |
አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ።