ዘፍጥረት 19:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱ ሰዎችም ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በከተማዪቱ ውስጥ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ዐማቾች፣ ወንዶችና ሴቶች ወይም ሌሎች ዘመዶች ካሉህ ቶሎ ብለህ ከዚህ እንዲወጡ አድርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት፦ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ ብትሆን በከተማይቱ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱም እንግዶች ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በዚህች ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ የልጆችህ እጮኛዎችና ሌሎች ዘመዶች ቢኖሩህ ከዚህች ከተማ በፍጥነት እንዲወጡ አድርግ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም መላእክት ሎጥን አሉት፥ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን፥ ወንድ ልጅም ቢሆን፥ ሴት ልጅም ብትሆን፥ በዚህ ከተማ የምታውቀው ወዳጅ ቢኖርህ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን ውንድ ልጅም ቢሆን ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ ብትሆን በከተማይቱ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸ |
ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹ እጮኞች የሆኑትን ዐማቾቹን፣ “እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ሊያጠፋት ነውና በፍጥነት ከዚህ ስፍራ ውጡ” አላቸው፤ ዐማቾቹ ግን የሚቀልድ መሰላቸው።
እንዳወጧቸውም፣ መልአኩ፣ “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ፈጥናችሁ ሽሹ፤ መለስ ብላችሁ ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ከረባዳው ስፍራ እንኳ ቆም አትበሉ፤ ወደ ተራራው ሽሹ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ” አላቸው።
እርሱም፣ “ከእነዚህ ክፉ ሰዎች ድንኳን ራቁ የእነርሱ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትንኩ፤ አለዚያ በእነርሱ ኀጢአት ሁሉ እናንተም ትጠፋላችሁ” ሲል ማኅበሩን አስጠነቀቀ።
ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።