ዘፍጥረት 12:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም በግብጽ አገር እንደ ደረሰ ግብጻውያን፣ ሦራ እጅግ ውብ ሴት እንደ ሆነች አዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም ወደ ግብጽ በገባ ጊዜ የግብጽ ሰዎች ሴቲቱ እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ በእርግጥም ግብጻውያን የአብራም ሚስት በጣም ቈንጆ እንደ ሆነች አዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ አብራም ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ የግብፅ ሰዎች ሴቲቱን እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ የግብፅ ሰዎች ሴቲቱን እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፤ |
ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከርሷም ጋራ ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።