ዘፍጥረት 1:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ “ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን” አለ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፥ “በውኃው መካከል ጠፈር ይሁን፤ በውኃና በውኃ መካከልም ይለይ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፤ በዉኖች መካከል ጠፈር ይሁን በዉኂ መካከል ይከፈል አለ። |
እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱ ሕያው አምላክ፣ ዘላለማዊም ንጉሥ ነው፤ በሚቈጣበት ጊዜ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ መንግሥታትም ቍጣውን ሊቋቋሙ አይችሉም።
ስለ እስራኤል የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ፣ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ሰማያት ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው እንደሚኖሩ፣ መሬትም በውሃ መካከልና በውሃም እንደ ተሠራች ሆነ ብለው ይክዳሉ፤