ዘፍጥረት 1:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ ብርሃኑን ከጨለማ ለየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም፥ ብርሃን መልካም መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔርም ብርሃንን ከጨለማ ለየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚአብሔርም በብርሃኑና በጨለማው መካከል ለየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ። |
ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።
እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።