Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 1:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” ብሎ ሰየመው፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያ​ው​ንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራዉ የዉኂ መከማቻዉንም ባሕር አለዉ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 1:10
7 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ ብርሃኑን ከጨለማ ለየ።


የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይበለው፤


እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤


የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።


እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።


እርሱም፣ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አለ።


እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos