ዘፍጥረት 1:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፣ እጅግ መልካም ነበረ። መሸ፤ ነጋም፤ ስድስተኛ ቀን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፥ እጅግ መልካም ነበረ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱ ነጋ፤ ስድስተኛ ቀን ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የፈጠረውን ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኛም ቀን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚእብሔርም ያደረገዉን ሁሉ አየ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኚ ቀን። |
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፤ ባሕርንም በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሮ፣ በሰባተኛው ቀን ዐርፏልና። ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።
በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ለዘላለም ምልክት ይሆናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ሠርቶ፣ በሰባተኛው ቀን ከሥራ ታቅቦ ዐርፏልና።’ ”
ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ አምላክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም።