ዘፍጥረት 1:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፥ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ። |
እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃኑንም በላያችን አበራ፤ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በመውጣት፣ ዝንጣፊ ይዛችሁ በዓሉን ከሚያከብሩት ጋራ ተቀላቀሉ።
ከእንግዲህ በቀን የፀሓይ ብርሃን አያስፈልግሽም፤ በሌሊትም የጨረቃ ብርሃን አያበራልሽም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃን፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና።
በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቷልና።
ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።
እርሱ ብቻ ኢመዋቲ ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን። አሜን።
በሌላ በኩል የምጽፍላችሁ ጨለማው እያለፈና እውነተኛው ብርሃን እየበራ ስለ ሆነ፣ በርሱም፣ በእናንተም ዘንድ እውነት የሆነውን አዲስ ትእዛዝ ነው።