ዘዳግም 6:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር እንድትጠብቁት አስተምራችሁ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጠኝ ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህ በርስትነት በሚሰጥህ ምድር እንድትጠብቃት እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዝ፥ ሕግና ሥርዓት ይህች ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁን ተሻግራችሁ በርስትነት በሚሰጣችሁ ምድር እንድትጠብቁት እግዚአብሔር አምላክህ እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዞች፥ ሕግና ሥርዓት እነዚህ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉት ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዘው ትእዛዝና ሥርዐት፥ ፍርድም ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት። |
ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ፣ በሞዓብ ሜዳ ሳሉ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዞችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።
የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር፣ እንድትወርሷት በሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ ሁሉ፣ በጥንቃቄ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ሥርዐቶችና ሕግጋት እነዚህ ናቸው።
በዚያ ጊዜ እኔ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ለእናንተ ሰጥቷችኋል፤ ይሁን እንጂ የአካል ብቃት ያላቸው ሰዎቻችሁ ሁሉ ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ፊት በመቅደም መሻገር አለባቸው።
አሁንም እስራኤል ሆይ፤ በሕይወት እንድትኖሩ፣ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር እንድትገቡና እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ ጠብቋቸውም።
አንተ ግን እንዲወርሷት በምሰጣቸው ምድር እንዲጠብቋቸው የምታስተምራቸውን ትእዛዞች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች ሁሉ እንድሰጥህ እዚሁ ከእኔ ዘንድ ቈይ።”
በምትወርሷት ምድር በሕይወት ለመኖር እንድትችሉ፣ መልካም እንዲሆንላችሁና ዕድሜያችሁም እንዲረዝም፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።
ይኸውም፣ የምሰጣችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፣ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም፣ አንተ፣ ልጆችህና ከእነርሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቻቸው በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትፈሩት ዘንድ ነው።