ዘዳግም 5:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባውም ከአባቶቻችን ጋራ ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ በሕይወት ከምንገኘው ከእኛ ከሁላችን ጋራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ይህችን ቃል ኪዳን ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን ያደረገው ዛሬ በዚህ በሕይወት ካለነው ከእኛ ከሁላችንም ጋር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃል ኪዳን ያደረገውም ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን፥ አሁን በሕይወት ካለነውም ከእኛ ሁሉ ጋር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ዛሬ በዚህ በሕይወት ካላችሁት ከእናንተ ከሁላችሁ ጋር እንጂ ከአባቶቻችሁ ጋር ይህችን ቃል ኪዳን አላጸናም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ዛሬ በዚህ በሕይወት ካለነው ከእኛ ከሁላችን ጋር እንጂ ከአባቶቻችን ጋር ይህችን ቃል ኪዳን አላደረገም። |
በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ከግብጽ አወጣቸው ዘንድ፣ እጃቸውን ይዤ በመራኋቸው ጊዜ፣ ከአባቶቻቸው ጋራ እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ የእነርሱ ባል ሆኜ ሳለሁ፣ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና።” ይላል እግዚአብሔር።
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በባርነት ከተገዙበት ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ፣ ከአባቶቻችሁ ጋራ እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ፤
እግዚአብሔር በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋራ እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።