ዘዳግም 28:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማ ትባረካለህ፣ በዕርሻህም ትባረካለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በከተማ ትባረካለህ፥ በዕርሻህም ትባረካለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ከተሞችህንና እርሻዎችህን ይባርካል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፤ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ። |
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ባረከ፤ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
በጐተራ የቀረ ዘር አሁንም ይገኛልን? የወይኑና የበለሱ ዛፍ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ እስካሁን አላፈሩም። “ ‘ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’ ”