ዘዳግም 24:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ፣ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፣ የፍች ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባት በኋላ፥ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፥ የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ እርስዋን የማይወድበትን ነገር በማግኘቱ ቢጠላት የፍች የምስክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያባርራታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንድ ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፤ ከቤቱም ይስደዳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍች ወረቀት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው? እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፣ እርሷም ሄዳ ሌላ ሰው ብታገባ፣ ወደ እርሷ ይመለሳልን? ምድሪቱስ ፈጽማ አትረክስምን? አንቺ ግን ከብዙ ወዳጆችሽ ጋራ አመንዝረሻል፤ ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽን?” ይላል እግዚአብሔር።
ለከዳተኛዪቱ እስራኤል ስለ ምንዝርናዋ ሁሉ የፍች ወረቀቷን ሰጥቼ አባረርኋት። ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አይታ እንዳልፈራች አየሁ፤ ወጥታም አመነዘረች።
“ፍችን እጠላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፤ “ልብሱን በግፍ ድርጊት የሚሸፍነውንም ሰው እጠላለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ታማኝነታችሁም አይጓደል።
አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፣ አንደኛዋን የሚወድዳት፣ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፣ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኵር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወድዳት ሚስቱ ቢሆን፣
ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፤ ገንዘቡንም ለልጅቱ አባት ይስጡት፤ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።
ሰውየው ለልጅቱ አባት ዐምሳ ሰቅል ብር ይክፈል፤ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሯታልና፣ እርሷን ማግባት አለበት፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።