“እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ግዛታቸውን እንዳይወርሩባቸው በማድረግህ ከእነርሱ ተመልሰው ሳያጠፏቸው የቀሩት የአሞን፣ የሞዓብና የሴይር ተራራ ሰዎች እነሆ እዚህ አሉ።
ዘዳግም 2:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሞዓባውያን ምድር አንዳችም መሬት ስለማልሰጣችሁ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው፤ ዔርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ ‘የሎጥ ዘሮች የሆኑትን ሞአባውያንን አታስቸግሩ፤ ከእነርሱም ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ የዔርን ከተማ ለእነርሱ መኖሪያ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህም ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁም።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓብን አትጣላ በሰልፍም አትውጋቸው። |
“እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ግዛታቸውን እንዳይወርሩባቸው በማድረግህ ከእነርሱ ተመልሰው ሳያጠፏቸው የቀሩት የአሞን፣ የሞዓብና የሴይር ተራራ ሰዎች እነሆ እዚህ አሉ።
ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤ የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤ በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች። የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣ በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።
ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣
በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ ሞዓባውያን እንዳደረጉልን ሁሉ፣ አንተም አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክንሻገር ድረስ እንደዚሁ አድርግልን።”
ከየትኛውም ምድራቸው ላይ ለጫማችሁ መርገጫ ታኽል እንኳ መሬት ስለማልሰጣችሁ፣ ለጦርነት አታነሣሧቸው። ኰረብታማውን የሴይርን አገር ርስት አድርጌ ለዔሳው ሰጥቼዋለሁ።
እስራኤልም ወደ ኤዶም ንጉሥ፣ ‘በአገርህ እንዳልፍ እባክህ ፍቀድልኝ’ በማለት መልእክተኞችን ላከበት፤ የኤዶም ንጉሥ ግን አልሰማውም። ለሞዓብ ንጉሥም እንደዚሁ ላከበት፤ እርሱም አልተቀበለውም፤ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ።
“ቀጥሎም የኤዶምንና የሞዓብን ምድር በመዞር፣ በምድረ በዳው ተጕዞ ከሞዓብ በስተምሥራቅ በኩል በማለፍ ከአርኖን ማዶ ሰፈረ፤ የሞዓብም ድንበር አርኖን ስለ ነበር ወደ ሞዓብ ክልል አልገባም።