እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአኪያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ስለ ወሰነ፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።
ዘዳግም 2:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላካችሁ እግዚአብሔር አሁን እንዳደረገው ሁሉ እርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ለመስጠት መንፈሱን አደንድኖት፣ ልቡንም አጽንቶት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፥ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ መንፈሱን አደንድኖታልና ልቡንም አጽንቶታልና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን ሲሖን ንጉሥ ሴዎን በእርሱ ግዛት ውስጥ አልፈን እንድንሄድ ባለመፍቀዱ፥ አሁን እንዳደረገው አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሊሰጠው ስለ ፈቀደ ትዕቢተኛና እልኸኛ አደረገው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና። |
እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአኪያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ስለ ወሰነ፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።
እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአኪያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ስለ ወሰነ፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።
ሙሴና አሮንም እነዚህን ድንቅ ታምራት በፈርዖን ፊት አደረጉ። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ ፈርዖንም እስራኤላውያን ከአገሩ ለቅቀው እንዲሄዱ አልፈቀደም።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ወደ ግብጽ በምትመለስበት ጊዜ በሰጠሁህ ኀይል የምትሠራቸውን ታምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ። እኔ ግን ሕዝቡን እንዳይለቅ ልቡን አደነድነዋለሁ።
ሴዎን ግን እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዲያልፍ አልፈቀደም፤ ሰራዊቱን በሙሉ አሰባስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ወጣ፤ ያሀጽ እንደ ደረሰም ከእስራኤል ጋራ ጦርነት ገጠመ።
እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እርሱን ከመላው ሰራዊቱና ከምድሩ ጋራ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን ሁሉ በርሱም ላይ አድርግበት” አለው።
እግዚአብሔርም፣ “እነሆ፤ ሴዎንንና አገሩን ለእናንተ አሳልፌ ልሰጣችሁ ተነሥቻለሁ፤ አሁንም እርሱን አሸንፋችሁ ምድሩን ለመውረስ ተነሡ” አለኝ።